ቀጥታ፡

በትምህርት ዘመኑ የተሻለ ዕውቀት ለመጨበጥ ትምህርታችንን በትጋት እየተከታተልን ነው

አዲስ አበባ፤መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፦በተያዘው የትምህርት ዘመን የተሻለ ዕውቀትና ክህሎት ለመጨበጥ ትምህርታቸውን በትጋት እየተከታተሉ መሆናቸውን  በአዲስ አበባ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ

የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ለማሻሻል ንድፈ ሐሳብን ከተግባር ጋር ያጣመረ የመማር ማስተማር ምኅዳር በመፍጠር ትምህርት እየተሰጠ  መሆኑን የትምህርት ቤት መምህራንና ርዕሳነ መምህራን አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በሁለቱ ቤቶች የጋራ ስብሰባ የመንግሥትን የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ይፋ ሲያደርጉ በጀት ዓመቱ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ትኩረት የሚደረግበት ነው።

በሁለቱ ቤቶች የጋራ ስብሰባ የመንግሥትን የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ይፋ ሲያደርጉ በጀት ዓመቱ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ትኩረት የሚደረግበት መሆኑን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱም በማኅበራዊ መስክ በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ ብቁ ዜጋን ለማፍራት፣ ትውልድን የሚቀርጽ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በቁልፍ ጉዳይነት የሚሠራበት መሆኑን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፣ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ብቁ ዜጋን ማፍራት የሚያስችሉ ናቸው።

በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት መምህራን በማስተማር፣ ተማሪዎች ደግሞ በትጋት በማጥናት ውጤታማ የትምህርት ዘመን ለማሳለፍ እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሙሉዓለም መለሰ እንዳለው፣ መደበኛ የመማሪያና አጋዥ መጽሐፍትን በማጥናት ትምህርቱን በትጋት እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

በትምህርት ቤቱ የ11ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ብርቱካን እውነቱ በበኩሏ፣ ከመደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ በዲጂታልና ሌሎች አማራጮች ዕውቀትና ክህሎቷን እያዳበረች መሆኗን ተናግራለች።


 

ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተናን በብቃት ማለፍ የሚያስችለኝን ዝግጅት ከወዲሁ እያደረኩ ነው ያለው ደግሞ በድልበር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪ ተስፋ ዋጋዬ ነው።


 

ለዚህም የትምህርት ዘመኑን የመልቀቂያ ፈተና ለማለፍ ከመደበኛ መማር ማስተማር ባሻገር በማጠናከሪያ ትምህርትና በቤተ-መጽሐፍት ጥናት ራሱን እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።

በትምህርት ቤቱ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ በአምላክ ቸርነት በበኩሏ፣ በትጋት ማጥናት የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ በመጠቆም፣ ለዚህም እርስ በእርስ በመተጋገዝ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን ተናግራለች።


 

የድልበር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ሀብታሙ ግዛው እንዳሉት፣ የተማሪዎችን ዕውቀት የሚያንጽ ቀላልና ግልጽ የመማር ማስተማር ሥነ-ዘዴ እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።


 

የለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ኃይማኖት በጋሻው በበኩላቸው፣ የተማሪዎችን የትምህርት ተወዳዳሪነት በማላቅ፣ በዕውቀትና ክህሎት የዳበረ ትውልድ ለማፍራት በኃላፊነት እየሰራን ነው ብለዋል።


 

የለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር ሰለሞን ዲሮ፣ ከትምህርት ማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር የትምህርት ውጤታማነትን ለማሻሻል በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል።



በዘንድሮው የትምህርት ዘመንም የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ለማሻሻል የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት፣ ተማሪዎች በመደበኛና በማጠናከሪያ ትምህርት ራሳቸውን እንዲያበቁ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የድልበር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር ደጀኔ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ለተማሪዎች ንድፈ ሐሳብን ከተግባር ጋር ያጣመረ ትምህርት እየተሰጠ ነው ብለዋል።


 

በ2019 የትምህርት ዘመን ቤተ-ሙከራ፣ ቤተ-መጽሐፍትና ሌሎች ግብዓቶችን በማሟላት፣ የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ የሚያጠናክር የመማር ማስተማር ምኅዳር መፈጠሩን ገልጸዋል።

ወላጆችም ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ሚናቸውን መወጣት፣ እንዲሁም የልጆቻቸውን የትምህርት አቀባበል በትኩረት መከታተል እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም