ቀጥታ፡

አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን በመርታት ወደ አሸናፊነት ተመለሰ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 30 /2019 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሃ ግብር አርሰናል ከመመራት ተነስቶ ሊድስ ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጀምስ ጀስቲን በ55ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ሊድስ መሪ ሆኗል።’

ሪካርዶ ካላፊዮሪ በ62ኛው እና ብሩኖ ጉማሬሽ በ70ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ግቦች አርሰናል ድል ቀንቶታል።

ተቀይሮ የገባው ጉማሬሽ ያስቆጠረው ጎል  ድንቅ የሚባል እና ውበት ያለው የቡድን እንቅስቃሴ የታየበት ነው።

የወቅቱ ሻምፒዮን አርሰናል በሁለተኛ አጋማሽ ያሳየው የተሻለ እንቅስቃሴና የፈጠራቸው የግብ እድሎች አሸናፊ አድርገውታል።

ወደ አሸናፊነት መንገድ የተመለሰው አርሰናል በ15 ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ባለው ማንችስተር ሲቲ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊድስ ዩናይትድ በዘጠኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም