ቀጥታ፡

በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ እየተጓጓዘ ነው

ሰመራ ፤መስከረም 30/2019 (ኢዜአ) ፦ በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማእከላዊ መጋዘን የተጫነ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ወደ አፋር ክልል በመጓጓዝ ላይ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።


 

ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክልሎች በራሳቸው አቅም ምላሽ ለመስጠት እየተረባረቡ ሲሆን ኮሚሽኑም የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

በዚሁ መሰረትም በአፋር ክልል የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ በማድረስ ላይ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የአፋር ክልል በራሱ አቅም የሚያደርገው ድጋፍና ክትትል እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽኑም የቅርብ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ከአዳማ የመጠባበቂያ መጋዘን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ የአፋር ክልል ተንቀሳቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም