የ'ሆራ አየቱ' ኢሬቻ በዓል በአምቦ ከተማ ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
የ'ሆራ አየቱ' ኢሬቻ በዓል በአምቦ ከተማ ተከበረ
አምቦ፤መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፡- የ'ሆራ አየቱ' ኢሬቻ በዓል አባ ገዳዎች፣ሃዳ ስንቄዎች እና በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በተገኙበት በአምቦ ከተማ ተከበረ።
የ'ሆራ አየቱ' ኢሬቻ በዓል ላይ የተገኙት የቱላማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ፤ የኢሬቻ በዓል በአብሮነት በመሰባሰብ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት የፍቅርና መልካምነት እሴት መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም የበዓሉን እሴት ጠብቆ ማክበርና ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል ሀዳ ስንቄ አየሉ ዊርቱ፤ የ'ሆራ አየቱ' ኢሬቻ በዓል የአብሮነት፣ የሰላም፣ የፍቅርና የመልካም ተስፋ መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢሬቻ በዓል አከባበር ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው አምላክ ምስጋና የሚቀርብበት ስለመሆኑ አንስተው በዓሉን በመጠበቅ እና በመከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ይገባል ብለዋል።
የኢሬቻ በዓል በየዓመቱ በአዲስ አበባ (ሆራ ፊንፊኔ) እንዲሁም በቢሾፍቱ (ሆራ አርሰዲ) ከተከበረ በኋላ በየአካባቢው መከበሩን የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው እለትም በአምቦ ሆራ አየቱ የኢሬቻ በዓል ተከብሯል።