በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል - ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን - ኢዜአ አማርኛ
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል - ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው በሰጡት መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መንግስት ወደ አዘጋጀላቸው ማዕከላት ለመግባት ጥሪውን እየተጠባበቁ ነው።
ስለሆነም የተሃድሶ ኮሚሽኑ ታጣቂዎችን በመቀበል ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል።
ታጣቂዎች ኮሚሽኑ ባዘጋጃቸው የቅበላ ማዕከላት በመምጣት ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲገቡ ጥሪ አቅርቧል።
መንግስት በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የቅበላ ማዕከላትን ማዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በደቡባዊ ዞን በማይጨው እና መሆኒ ከተሞች፤ በደቡብ ምስራቅ ዞን በመቀሌ ከተማ በሚገኙ ማዕከላት እንዲገቡ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ ጠይቀዋል።
በምስራቃዊ ዞን በአዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች፤ በማዕከላዊ ዞን አድዋ፣ አክሱም እና አቢአዲ ከተሞች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ ዞን ሸሬ ከተማ ወደ አሉት የቅበላ ማዕከላት እንዲገቡ ጥሪ አድርገዋል።
በዚህም ታጣቂዎቹን የሚቀበሉ መዘጋጀታቸውን ጠቁመው ታጣቂዎች ይህንን ዕድል በመጠቀም ወደ ሰላማዊ ሕይወት በመምጣት እና ራሱን እንዲያድንም ጥሪ አቅርበዋል።
በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ጽንፈኛውን ቡድን እየተቃወመ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ተዘጋጁት ማዕከላት በመግባት ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ከማድረግ አኳያ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።