ቅዱስ ጊዮርጊስ ከነገሌ አርሲ: የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብር - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከነገሌ አርሲ: የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብር
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ሁለት ጨዋታዎች ያደረጋሉ።
ከቀኑ 9 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከነገሌ አርሲ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
የ16 ጊዜ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2018 የውድድር ዓመት በ54 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው።
አምና ወደ ሊጉ ያደገው ነገሌ አርሲ በመጀመሪያ ዓመቱ 60 ነጥብ በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።
ሁለቱ ክለቦች ባለፈው የውድድር ዓመት ባደረጓቸው የሊግ ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንዱ ድል ሲቀናው በቀሪው ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በ2018 የውድድር ዓመት ወላይታ ድቻ በ51 ነጥብ ሰባተኛ፣ ፋሲል ከነማ በ55 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው።
ክለቦቹ ባለፈው የውድድር ዓመት ሁለት ጊዜ ተገናኝተው ፋሲል ከነማ አንዱን ሲያሸንፍ በሌላኛው መርሐ ግብር ነጥብ ተጋርተዋል።