የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የሥራ ርክክብ አካሄዱ - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የሥራ ርክክብ አካሄዱ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሺዴ ከቀድሞው አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር የሥራ ርክክብ አካሂደዋል።
በርክክቡ ወቅትም አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ላለፉት አመታት የተጣለባቸውን ምክር ቤታዊ ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እና በመግባባት መንፈስ ተወጥተዋል።
ሁለቱም አፈ-ጉባኤዎች ለህዝብና ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ያመሰገኑት አቶ አሕመድ ሽዴ በቀጣይም ምክር ቤቱ የተጀመሩ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የቀድሞ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በምክር ቤት ቆይታቸው የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመወጣት የሪፎርም ስራዎችን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡
በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ምክር ቤቱን እና የምክር ቤቱን ጽሕፈት ቤት አመራሮችን በማመስገን፤ የ7ኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
በስራ ርክክቡ ወቅት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አየለች እሸቴ እና የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡