ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር(ዶ/ር) ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር(ዶ/ር) ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29 /2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር(ዶ/ር) እና ልዑካቸውን ዛሬ መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹትበቆይታችን በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን ጠንካራና የቆየ ወዳጅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልእክት ከሰሞኑ በሕንድ ካደረግኩት ጉብኝት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ከነበረኝ ቆይታ ተከትሎ በተጠናከረ ትብብርና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወዳጅነታችንን ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተነጋግረናል ብለዋል።