ቀጥታ፡

በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ እየተጓጓዘ ነው

አዳማ ፣መስከረም 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች መንግስት በራስ አቅም የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በዛሬው እለት ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማእከላዊ መጋዘን የተጫነ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ  ወደተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች በመጓጓዝ ላይ ይገኛል።

ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክልሎች በራሳቸው አቅም ምላሽ ለመስጠት እየተረባረቡ ሲሆን ኮሚሽኑም የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።


 

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ በማጠናከር ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የተለየ ትኩረት በመስጠት ሰብአዊ ድጋፍ የማድረስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ አመላክቷል።

ክልሎች በራሳቸው አቅም የሚያደርጉት ድጋፍና ክትትል እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽኑም የሚመከታቸውን የፌዴራል መንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች በማስተባበር የቅርብ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል።

በዛሬው እለትም ከአዳማ የመጠባበቂያ መጋዘን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች የቅድሚያ ቅድሚያ ወደተሰጣቸው አካባቢዎች ተንቀሳቅሰዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም