ኢትዮጵያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ስራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ስራ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ገለጹ።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አድርገዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በጉብኝቱ ወቅት ተቋሙ በአገልግሎት፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎች ዘርፎች የሰው ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ የምርምርና ልማት ስራዎች ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።
በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት እያከናወነ የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ስራዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ኢትዮጵያ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ስራ መሆኑን አመልክተዋል።
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት መጠናከር ለአፍሪካ የሚተርፍ ትሩፋት እንዳለው መግለጻቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመለክታል።