ሀላባ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ሀላባ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29 /2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ሀላባ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሽመክት ጉግሳ በ48ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ሀላባን መሪ አድርጓል።
ካርሎስ ዳምጠው በ94ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ ባሳረፋት ጎል ወልዋሎ አቻ ሆኗል።
አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ሶስት ነጥብ ሊያገኝበት የሚችልበትን እድል መጠቀም አልቻለም።
በፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፎ እያደረገ ያለው ሀላባ ከተማ የመጀመሪያ ነጥቡን አግኝቷል።
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ እየተሳተፈ የሚገኘው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ አንድ ነጥብ አሳክቷል።
ዛሬ በተደረገ የፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል።
የሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።