ቀጥታ፡

በሊጉ መክፈቻ ጨዋታ አዳማ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 29 /2019 (ኢዜአ)፦ በ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢንያም አይተን በ29ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ጎሏን አስቆጥሯል።

ቢንያም የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሁለተኛው አጋማሽ ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥሮ ቢጫወትም ሊሳካለት አልቻለም።

በፋሲል ተካልኝ የሚመራው አዳማ ከተማ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል።

የዘሪሁን ሸንጋታው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ሽንፈት አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም