የመደመር መንግሥት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው- ምሁራን - ኢዜአ አማርኛ
የመደመር መንግሥት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው- ምሁራን
ሰመራ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦የመደመር መንግስት ገቢር ነበብ የዲፕሎማሲ አካሄድና የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ የጎረቤት አገራትን በማስቀደም አብሮ መልማትንና የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ ባደረገ መልኩ በስኬታማነት ቀጥሏል።
በኤሌክትሪክ ኃይል የልማት ትስስር፣ በአረንጓዴ አሻራ እና ሌሎችም ዘርፎች የአካባቢውን አገራት የጋራ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
ከዚሁ በተጓዳኝ የኢትዮጵያን ታሪካዊ፣ ህጋዊና መልካአ ምድራዊ የባህር በር ባለቤትነት መብቷን ለማስከበር የሚያስችል የዲፕሎማሲ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል።
በመሆኑም የመደመር መንግስት ገቢር ነበብ የዲፕሎማሲ አካሄድና የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ኃላፊ ሙክታር ጦይብ፤ የመንግሥት የዲፕሎማሲ ጥረትና እየተከተለው ያለው መርህ የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም መሰረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ የተደረገችበትን የሚያስቆጭ አጋጣሚ በሰጥቶ መቀበል የዲፕሎማሲ ጥረት ለማስተካከል ለሚደረገው ጥረት ክብር ይገባል ብለዋል።
እንደ አጠቃላይ የመደመር መንግስት ገቢር ነበብ የዲፕሎማሲ አካሄድና የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሕግና አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህሯ እታለም ወንዱ፤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በሰጥቶ መቀበል የዲፕሎማሲ መርህ የሚደረገው ጥረት ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።
ለዜጎች ክብርና ደህንነት በማሰብ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም የሚያስመሰግን አካሄድ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ የመደመር መንግስት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ምሁራኑ ገልጸዋል።