የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ጅማሮውን ያገኛል።
የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ በኢትዮ ኤሌክትሪክና አዳማ ከተማ መካከል ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
በ2019 ዓ.ም የውድድር ዓመት ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ54 ነጥብ አምስተኛ፣ አዳማ ከተማ በ46 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው።
በሌላኛው መርሐ ግብር አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከቀኑ 10 ሰዓት በሃላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይጫወታሉ።
ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ ጥቅምት 1 2019 ዓ.ም ይቆያል።
የሊጉ ጨዋታዎች በሰባት የተመረጡ ስታዲየሞች ይደረጋሉ።
አዲስ አበባ ስታዲየም፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፤ ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም፣ሀላባ ስታዲየም፣ ሆሳዕና አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም እና አርባምንጭ ዩንቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም ውድድሩ የሚካሄድባቸው ሜዳዎች ናቸው።
በውድድሩ ላይ 18 ክለቦች ይወዳደራሉ።