የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 28 /2019(ኢዜአ) ፦የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ፤ ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘመናት የተሻገረና ሁለንተናዊ የሁለትዮሽ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ውጤታማ ውይይቶች የሚካሄዱበት እንደሚሆን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
#የመደመርመንግሥት