ካናዳ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈች - ኢዜአ አማርኛ
ካናዳ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 28 /2019 (ኢዜአ)፦ ካናዳ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፋለች።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
በዚህም ካናዳ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክቷን አስተላልፋለች።
በኢትዮጵያና በቀጣናው ሀገራት ከፍተኛ ለውጦች እየታዩ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ ካናዳ ከአዲሱ መንግሥት ጋር በመሆን የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።
በተጨማሪም ሰላምን፣ ደህንነትን፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትንና ቀጣናዊ መረጋጋትን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን ለመደገፍ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ፍላጎት እንዳላትም አስታውቃለች።