ቀጥታ፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ሙሀመድ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 28 /2019 (ኢዜአ)፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ሙሀመድ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።


 

ሚኒስትር ዴኤታው የምክትል ዋና ፀሐፊዋ ጉብኝት ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመምከርና ዕድሜ ጠገብ የሆነውን አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተጨማሪ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም