ቀጥታ፡

ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

መስከረም 28/2019 (ኢዜአ) ፡-የመደመር መንግስት፤ ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት እጩ የካቢኔ አባላትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ሹመታቸውን አጸድቀዋል።

የካቢኔ አባላቱ ሹመት ህዝብን የማገልገል አቅምና ፍላጎት፤ የትምህርት ዝግጁነት፣ የስራ ልምድና አጠቃላይ ውጤታማነትን መሰረት ያደረገ ነው።

እንደ አጠቃላይ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የከፍታ ምዕራፍ የማሸጋገር አደራና ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

በቀጣይ በላቀ የስራ አፈፃፀም የሀገርን እድገት የማስቀጠልና በዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት በሚታይ ለውጥ ለማምጣት መትጋትም ይጠበቅባቸዋል።

በተቋማት ቀጣይነት፣ በሥርዓት ግንባታና በሕዝብ አገልግሎት ውጤታማነት ላይ በመመሥረት የሀገር ግንባታን ሂደት ማስቀጠል የመደመር መንግስት አበይት ትኩረቱ አድርጎ እንደሚሰራም ይጠበቃል።

የተቋማት ስኬት የሚለካው ለሕዝብ በሚሰጡት ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሁም ውጤታማ አገልግሎት በመሆኑ ሚኒስትሮቹ በዚሁ ልክ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።

የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የህዝብ እውነተኛ አገልጋይ ለመሆን የሚተጉ መሆን ይኖርባቸዋል።

የመደመር መንግስት የካቢኔ አባላት እጩዎችም የመፈጸም አቅምና ፍላጎት፣ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት እንደ መሠረታዊ መስፈርቶች ተወስደው የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የህዝብ እውነተኛ አገልጋይ ለመሆን በመዘጋጀት መሆኑን እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል።

የመንግስት ሹመት “የሚዝናኑበት ሳይሆን የሚሰሩበት” ከፍተኛ የሕዝብ አደራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የካቢኔ አባላት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል እንዲተጉም አሳስበዋል።

የመደመር መንግስት ሀገር የመምራት እድልም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የማስቀጠል፣ የተቋማትን ግንባታ የማጠናከር፣ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማስቀጠል ይሆናል። 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም