የኦሮሚያ ክልል አዲሱ የዞኖች አደረጃጀት ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኦሮሚያ ክልል አዲሱ የዞኖች አደረጃጀት ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው
ነገሌ ቦረና፣ መስከረም 28/2019(ኢዜአ)፡- የኦሮሚያ ክልል አዲሱ የዞኖች አደረጃጀት ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች አደረጃጀትን በተመለከተ የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ለኢዜአ ሰጥተዋል፡፡
የከተማው ነዋሪ አቶ ሽምብራ ጋረደው አደረጃጀቱ የህብረተሰቡን አብሮነት በማጠናከር የሰላምና የልማት ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል፡፡
ይህም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በህዝብ ተሳትፎ ለመስራትና በጋራ ለመልማት ተደማሪ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
አዲሱ አደረጃጀት ሀብትንና የሰው ሀይልን በማቀናጀት ልማቶች የሚፋጠኑበትንና ማህበራዊ አገልግሎትን ለማስፋት እንደሚያስችል የገለጹት ደግሞ ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ባጫ ጅማ ናቸው።
አደረጃጀቱ የህብረተሰቡ የአብሮነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚኒት ይበልጥ እንዲረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ለስኬታማነቱ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የከተማው ነዋሪ አቶ ሀይሉ ተሬ በበኩላቸው አደረጃጀቱ ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት የተሻለ አቅም ይፈጥራል የሚል ተስፋ ማድርጋቸውን ገልጸዋል።
በተለይም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የመተጋገዝ ባህላዊ እሴቶችን የሚያሳድግ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡