ቀጥታ፡

የተቀበልኩት ሕዝብና ሀገርን የማገልገል ከባድ ኃላፊነት ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተቀበልኩት ሕዝብና ሀገርን የማገልገል ከባድ ኃላፊነት ነው አሉ፡፡

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በድጋሚ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተቀበልኩት ሕዝብና ሀገርን የማገልገል ከባድ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን በምችለው ሁሉ በማገልገል ኃላፊነቴን እንድወጣ የሁላችሁም ድጋፍና ጸሎት አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ የማገልገልን ዕድል ዳግም አግኝቻለሁ ነው ያሉት።

#የመደመር_መንግሥት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም