የአውሮፓ ህብረት አዲስ ለተቋቋመው መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ - ኢዜአ አማርኛ
የአውሮፓ ህብረት አዲስ ለተቋቋመው መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 28 /2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ህብረት አዲስ ለተቋቋመው የኢትዮጵያ መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
ህብረቱ ባወጣው መግለጫ፤ አዲሱ መንግሥት የኢትዮጵያን ሕዝብ በማገልገልና ለሀገሪቱ ሰላማዊ፣ የተረጋጋ እና የበለጸገ መሠረት ለመጣል በሚያደርገው ጥረት ስኬት እንዲገጥመው ተመኝቷል።