ቀጥታ፡

የዛሬ የመደመር ካቢኔ ተሿሚዎች ህዝብ በምርጫ የሰጠውን አደራ በብቃት መሸከም የሚችሉ እንዲሆኑ ጥረት ተደርጓል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤መስከረም 28 /2019(ኢዜአ)፦ የዛሬ የመደመር ካቢኔ ሆነው የሚሾሙ ሚኒስትሮች ህዝብ በምርጫ የሰጠውን አደራ በብቃት መሸከም የሚችሉ እንዲሆኑ ጥረት መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ካቢኔያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ54 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በፈተና እና በመከራ ውስጥ መንግስት ለማጽናት ያለውን ቁርጠኝነት በማሳየት ከፍተኛ አደራ መስጠቱን ገልጸዋል።

ዛሬ የሚቀርበው የመደመር መንግስት ካቢኔ ይሄን የህዝብ ከፍተኛ አደራ የሚሸከም እንዲሆን ጥረት መደረጉን አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ አባላትን ለመምረጥ ገቢራዊ የተደረጉ መስፈርቶችን ሲያብራሩ የትምህርት ዝግጅት፤
የስራ ልምድና የተሻለ የስራ አፈጻጸም እንዲሁም በቀጣይ የሚሰጣቸውን ኃላፊነት የመፈጸም ብቃት ያላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጣቸውን አደራ እና ታላቅ ኃላፊነት ተገንዝበው ቀን ከሌት የሚሰሩ፣ ሙስናን የሚፀየፉና ለመከላከል ከፍተኛ ትግል የሚያደርጉ ፣ሕዝብን ማገልገል ጸጋ ነው ብለው የሚያምኑ እንደሆኑም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ያዘጋጀቸውን የ2050 የመደመር ታላቅ ስትራቴጂ በቅጡ የተረዱና የተቀመጡትን አበይት ነጥቦችና እሳቤያቸውን የተረዱ የብሔር ፤የጾታ፣ እና የእምነት ስብጥር ያላቸው ፣ ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን አውቅው የሚተጉ እነደሆኑም አስረድተዋል።

ካቢኔው ሁሉን አካታች እንዲሆን ጥረት መደረጉን ገልጸው ዛሬ የሚሾሙ ሚኒስትሮች ሹመት ድሎት ሳይሆን በልፋትና በትጋት ሀገርን ማገለገል መሆኑን በመገንዘብ በታማኝነት እንዲያገለግሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም