ቀጥታ፡

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፤መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድጋሚ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ስትራቴጂያዊ አጋርነት ትልቅ  ክብር እንደምትሰጥ ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አክለውም የሁለቱን ሀገራት ትብብርና ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

 #የመደመር_መንግሥት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም