ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፤መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በመንግሥት አስተዳደር ውስጥ ለ25 ዓመታት በማገልገል የብር ኢዮቤልዩአቸውን እያከበሩ ላሉት የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ናሬንድራ ሞዲ እአአ ከ2001 እስከ 2014 የጉጃራት ግዛት ዋና አስተዳዳሪ፣ ከዚያ ወዲህ ደግሞ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ እና የሕንድ አጋርነት ባለፉት ዓመታት ይበልጥ እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል።
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም