ኢትዮጵያ ሩዋንዳን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ሩዋንዳን አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ሩዋንዳን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በኢጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሩዋንዳዋ ኡዛዬሴንጋ ሊድያ በ45ኛው ደቂቃ በራሷ ላይ ያስቆጠረችው ግብ ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርጓል።
ይህም ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሏን አስፍቷል።
የሁለቱ ሀገራት የመልስ ጨዋታ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።
በደርሶ መልስ ውጤት ሉሲዎቹ ካሸነፉ ሶስተኛውን ዙር ይቀላቀላሉ።
በአምስት ዙሮች በሚካሄደው ማጣሪያ ሁለት ሀገራት አፍሪካን ወክለው በኦሊምፒክ ውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ።
በአጠቃላይ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ 12 ሀገራት የሚሳተፉ ይሆናል።