ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2019(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት እና የላቀ አመራር ልምድ ልውውጥ ላይ የሚሳተፈውን ልዑክ ከመሩት የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።


 

ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የበርካታ ብሔረሰቦች፣ የብዙ ባህሎች እና የከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር ባለቤት የሆኑ ሀገራት መሆናቸውን አመልክተዋል።


 

ይህም የሁለቱን ሀገራት ትብብር አጠናክረን ለማስቀጠልና የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መልካም ዕድል ይሰጠናል ሲሉም ተናግረዋል።

#ትልቅሀገር፣ #ትልቅሕዝብ፣ #ታላቅርዕይ

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም