የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26/2019/ (ኢዜአ) ፦የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማና ልዑካቸው አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
ጉብኝቱ ሀገራቱ ያላቸውን ተሞክሮ እንዲጋሩና የሁለትዮሽ ትብብሩን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚያስችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡