ቀጥታ፡

የአዲስ አበባን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት የበለጠ ስኬትና ውጤት እንድታስመዘግቡ እንመኛለን-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤መስከረም 26/ 2019 (ኢዜአ) ፦የአዲስ አበባን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት የበለጠ ስኬትና ውጤት እንድታስመዘግቡ እንመኛለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ዓመታት ለአዲስ አበባ በትጋትና በቁርጠኝነት ያገለገላችሁ አመራሮቻችንን፣ ወደ ሌላ አዲስ የኃላፊነት ቦታ በመመደባቸዉ በክብር ሸኝተናል ብለዋል።

በአዲስ አበባ የነበረን የጋራ አመራር፣ የጋራ ጥረትና የጋራ አሻራችን ሁሌም ይኖራል።ለሰጣችሁት አገልግሎት፣ ለከተማችን ልማት ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ከልብ እናመሰግናለን ነው ያሉት።

ከንቲባዋ በሄዳችሁበት ሁሉ፣ የአዲስ አበባን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት የበለጠ ስኬትና ውጤት እንድታስመዘግቡ እንመኛለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ አዲስ ኃላፊነት ተረክባችሁ የመጣችሁ አመራሮች፣ እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን አዲሱን የኃላፊነት ምዕራፍ በትጋት፣ በአንድነትና በጋራ አመራር፣ ለአዲስ አበባ ሕዝብ የበለጠ የሚታይ ለውጥና የላቀ ውጤት የምናስመዘግብበት ይሁን በማለት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም