የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
ይህን ተከትሎም የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ላለው የኢኮኖሚ እድገት አድናቆት ገልጸዋል።
ጅቡቲ ሁለቱ እህትማማች ሀገራት ያላቸውን ወዳጅነት እና አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።