ቀጥታ፡

የዛምቢያው ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦የዛምቢያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው በራሳቸው፣ በዛምቢያ መንግሥትና ሕዝብ ስም የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመልእክታቸው ዛምቢያ በሁለቱ ሀገራትና ሕዝቦች መካከል ባለው አክብሮትና የአፍሪካውያን አህጉራዊ ወንድማማችነት ላይ የተገነባውን ጠንካራና ወዳጃዊ ግንኙነት ከፍተኛ ዋጋ እንደምትሰጠው ገልጸዋል።

አክለውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ታሪካዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም ለጋራ ብልፅግናና ዕድገት የሚደረገውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲሱ የሥልጣን ዘመናቸው የስኬት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም