ቀጥታ፡

የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሀሰን ባስተላለፉት መልዕክት፣ በሀገራቸው መንግስት እና ህዝብ ስም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ደስ አለዎች ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

ይህ አዲስ የሥራ ዘመን ኃላፊነት ሕዝቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራር እና ለኢትዮጵያ ዕድገት ባላቸው ራዕይ ላይ ያለውን ትልቅ እምነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ እና ጥልቅ የወንድማማችነት ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ ገልጸው፤ የሁለቱ አገራት ሕዝቦች፣ የአገራቱ ብልጽግና እና የአፍሪካን አጠቃላይ እድገት መሰረት ባደረገ መልኩ ይህን ትብብር አጠናክሮ ለመቀጠል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም