አትሌት ትዕግስት አሰፋ የዓለም የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት እጩ ሆነች - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ትዕግስት አሰፋ የዓለም የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት እጩ ሆነች
አዲስ አበባ፤መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦አትሌት ትዕግስት አሰፋ የ2026 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች።
የዓለም አትሌቲክስ በሁለቱም ጾታዎች በተመሳሳይ 10 የዓለም ምርጥ አትሌት እጩዎችን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ከሴት እጩ አትሌቶች መካከል ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ትገኛለች።
አትሌት ትዕግስት ከዚህ ቀደም በእ.አ.አ በ2023 እና በ2025 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት እጩ እንደነበረች የሚታወስ ነው።
አትሌቷ በቅርቡ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በጉዳት ተፈትና 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ04 ሰከንድ በማጠናቀቅ የዓለም ሶስተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች ።
እንዲሁም በ2026 የለንደን ማራቶን በ2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በማጠናቀቅ የሴቶች ብቻ ማራቶን አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።