የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብል ምርት አቅም 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ማድረስ ተችሏል -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብል ምርት አቅም 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ማድረስ ተችሏል -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብል ምርት አቅም 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ማድረስ መቻሉን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባቸውን አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለምክር ቤቶቹ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ የእድገት እርምጃና ግስጋሴ የሚለካና በግልጽ የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል።
የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብል ምርት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል መድረሱን አመልክተዋል።
ይህም በ2011 ዓ.ም ከነበረው 335 ሚሊዮን ኩንታል ጋር ሲነጻጻር ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ጠቅሰዋል።
የሰብል ምርት እድገቱ ታላቅ እምርታ እና የኢትዮጵያ ልዕልናን በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን አመልክተዋል።