ቀጥታ፡

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጣቸው አዲሱ ኃላፊነት፣ ለሀገራቸው ባላቸው አርቆ አስተዋይነት እና ራዕይ ላይ ትልቅ እምነት መጣሉን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ሩቶ አክለውም፣ የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት ስኬታማ እንዲሆን በመመኘት፤ ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለሁለቱ አገራት እና ለቀጣናዊ ሰላምና ልማት የጋራ ጥቅሞች መረጋገጥ በትኩረት መሥራቷን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

#የመደመር_መንግሥት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም