ቀጥታ፡

በተያዘው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ10 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ በ2019 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ10 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባቸውን በማድረግ ላይ ናቸው።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለምክር ቤቶቹ ባደረጉት ንግግር በኢኮኖሚው መስክ ባለፉት አምስት ዓመታት አመርቂ የሚባሉ ውጤቶች መገኘታቸውን አመልክተዋል።

ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡ የኢኮኖሚ ስኬቶችም ለቀጣይ ስራ መሰረት መጣል የሚያስችሉ ጽኑ መሰረቶች ናቸው ብለዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት የ10 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

ይህንን የእድገት ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ ሁሉን አቀፍ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም