ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ ዓለም አቀፍ ተቀባይነቱ እያደገ መጥቷል- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ ዓለም አቀፍ ተቀባይነቱ እያደገ መምጣቱን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባቸውን በማድረግ ላይ ናቸው።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለምክር ቤቶቹ እያደረጉት ባለው የመክፈቻ ንግግር የኢትዮጵያ የልማት እና እድገት በዘላቂነት ለማስቀጠል ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ባህር ባር ማግኘት የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አመልክተዋል።

በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ አማራጭ የባህር በር ባለቤት ለመሆን ያላት ፍላጎት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲያድግ መሰረት መጣሉን ገልጸዋል።

ይህ የኢትዮጵያ መሻት ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋራ በጋራ የማደግና የመልማት ያላትን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።

የባህር በር ባለቤት የመሆን ጉዳይ በሰጥቶ መቀበል፣ በጋራ ተጠቃሚነት እና በሰላማዊ መንገድ እንዲሳካ ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም