ቀጥታ፡

ሁለቱ ምክር ቤቶች ዛሬ የጋራ ስብሰባቸውን ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ የጋራ ስብሰባቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በትላንትናው እለት አካሂዷል፡፡

በዚህም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡

የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ዛሬ ከደቂቃዎች በኋላ መካሄድ ይጀምራል።

#የመደመር_መንግሥት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም