የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፦ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር)ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸው ስኬት እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም፤ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በቀጣናውና በሕዝቦች መካከል ሰላም፣ መረጋጋት እና የጋራ ብልጽግና እንዲሰፍን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።