ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም -ፕሬዝዳት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም ሲሉ ፕሬዝዳት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

ፕሬዝዳት ታዬ አጽቀሥላሴ በመልዕክታቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በድጋሚ በመመረጥዎ የተሰማኝን ደስታ ልገልፅ እወዳለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም ሲሉ ተናግረዋል።

ታሪካዊቷ ሀገር ኢትዮጵያን ያገለግሉ ዘንድ የተሳካና ፍሬያማ የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ ከልብ እመኛለሁ በማለት መልካም ምኞታችውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም