ቀጥታ፡

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገቡ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፦ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ በመቀበላቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

‎ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።




ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ለአህጉሩ አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው ሲሉ ተናግረዋል።

አጋርነታችንን ይበልጥ ለማሳደግ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እንደምናጠናክር ተስፋ አለኝ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም