ቀጥታ፡

ሙስናን፣የዘመድ አሰራርን ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግሥት መራር እርምጃዎችን ይወስዳል 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርን፣ ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግስት መረር ያሉ እርምጃዎችን ይወስዳል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

በዚህም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርን፣ ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግስት መረር ያሉ እርምጃዎችን ይወስዳል ብለዋል።

እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያሉ ዘመናዊ አሰራሮችን እስከ ታችኛው እርከን በማድረስና የተጀመረውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥን የበለጠ ለማዘመን በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የመኖሪያ ቤት ችግሮችን ከስሩ ለመፍታትም አዳዲስ አካሄዶችን እንከተላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ የተገኙ ተሞክሮዎችን በማላቅ ጭምር የቤት ልማት መርሃ ግብር እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በዚህም የቤት ልማት መርሃ ግብር ውጤታማነትን በማሳደግ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ጊዜና ገንዘብ በሚቆጥብ በተጠናከረና ፈጣን አሰራር እንደሚተገብርም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም