ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ካለመችው ትልም ለአንዴ እንኳን ሸብረክ ሳትል ዕድገቷን ማስቀጠል ችላለች

አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የቸራትን የውሃ ሃብት አልምተን እንዳንጠቀም ሲያጋጥሙን የነበሩ ጫናዎችን በመሻገር ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ  እውን ማድረግ ችላለች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ

የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማፋጠን የሚያስችል መሰረት ተጥሏል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባሳለፈቻቸው ስኬታማ ዓመታትም ፈተናዎችን በብስለት በማለፍ  ሀገርን የሚቀይሩ የልማት ትሩፋቶች የተከናወኑበት መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት በቁርጠኝነት በሰራው ስራም ጠንካራ የፖለቲካልና  ኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት መቻሉን ተናግረዋል።

ዓለም ጀርባውን ሲያዞርብንና ፍርደ ገምድልነቱን ደግሞ ደጋግሞ ሲያሳየን ኢትዮጵያ ካለመችው ትልም ለአንዴ እንኳን ሸብረክ ሳትል ዕድገቷን ማስቀጠል እንደቻለችም አስረድተዋል።

ለዚህም ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የቸራትን የውሃ ሃብት አልምታ እንዳትጠቀም ሲያጋጥሙ የነበሩ ጫናዎችን በመሻገር ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ  እውን ማድረግ እንደተቻለ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም