ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሃሳቦች መሰረት የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ይኖራል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሃሳቦች መሰረት የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ እንደሚኖር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ

የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሄዷል።

አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፤ በቀጣዩ ጊዜያት በሀገራዊ የምክክር ምክረ ሀሳቦች መሰረት የሕገ-መንግስት ማሻሻያ ይኖረናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር በትብብርና ፉክክር ሚዛን ላይ ተመስርቶ እንዲቀጥል እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

በዚህም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በተለይም በምርጫ ሂደት ንቁ ተሳትፎ ከነበራቸው ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት መንግሥት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም