ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በእመርታ ወደፊት ትቀጥላለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በጽናት ተሻግራ በእመርታ ወደፊት ትቀጥላለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በመከናወን ላይ ይገኛል።

አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቱን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ብዙ ፈተናዎችን በጽናት ማለፏን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እድገት እና መስፈንጠር ያልተዋጠላቸው የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ሀገሪቱን ለማሰናከል እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የውስጥ ባንዳዎች ኢትዮጵያን አይችሏትም ከህልሟ ማንም አያሰናክላትም ሲሉም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ፍላጎቶቿን በራሷ አቅም እና ጉልበት ማሳካት እንደምትችል ማረጋገጧንም አመልክተዋል።

መንግስት ጠንካራና አይበገሬ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ስርዓት እየገነባ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ችግሮችና ፈተናዎችን በጽናት ተሻግራ ያሰበችው ቦታ መድረስ እንደምትችል አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም