ቀጥታ፡

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ

አዲስ አበባ፤መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፦ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል።

ግንቦት 24 2018 ዓ.ም የተካሄደውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ያሸነፈው ብልጽግና ፓርቲ መሆኑ ይታወሳል።

በዚህም 7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆኑትን ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ በሙሉ ድምፅ ሰይሟል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በመምራት ውጤታማ የአመራርነት ጥበባቸውን በተግባር አስመስክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ይበጃል ያሉትን የመደመር የፖለቲካ እሳቤ በማስተዋወቅና በህዝቡ ዘንድ እንዲሰርጽ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና ተወጥተዋል።

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁሉም ዘርፎች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲና በሌሎችም ዘርፎች ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየተጉ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም