ቀጥታ፡

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወ/ሮ አየለች እሸቴን በሙሉ ድምጽ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም የምክር ቤቱ አባላት ቃለ-መሀላ በመፈጸም ሥራቸውን በይፋ ጀምረዋል። 

እየተካሄደ በሚገኘው የመመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውም ወይዘሮ አየለች እሸቴን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ አድርጎ በሙሉ ድምጽ መርጧል፡፡

ወይዘሮ አየለች እሸቴ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሌሎች የመንግሥት ሃላፊነቶችም ስራቸውን በብቃት አከናውነዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም