ቀጥታ፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ለህዝብ የገባውን ቃል እንዲያሳካ ድጋፋችንን እናጠናክራል- ነዋሪዎች

ድሬደዋ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-አዲሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ለህዝብ የገባውን ቃል ዕውን እንዲያደርግ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ።

አዲሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምስረታና ለከተማዋ እድገትና መልካም አስተዳደር መስፈን ያላቸውን ተሳትፎ አስመልክተው አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ነዋሪዎች እንዳሉት፣ አስተዳደሩ በምርጫ ወቅት የገባውን ቃል ለማሳካት በሚያደርገው ጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ በንቃት ለመሳተፍ ተዘጋጅተዋል።

ከነዋሪዎች መካከል አቶ ዳንኤል ብርሃነ እንደተናገሩት፤ አዲሱ አስተዳደር የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን በላቀ ደረጃ እንዲፈጽም የድርሻቸውን ይወጣሉ።

ወይዘሮ ኤደን የሺጥላ እና አቶ ረመዳን ደስታ በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ በከተማዋ የሥራ ዕድል ፈጠራ ጥያቄን ለመመለስ እና የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ጠይቀው፣ ለዚህም የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አክለዋል።

አስተዳደሩ ያዋቀራቸው የሥራ ኃላፊዎች የሕዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በዕውቀት እና በሥራ ልምድ ብቁ መሆናቸውን መረዳታቸውንም ነው የገለጹት። 

የሚፈልጉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ውጤቶች ለማምጣትም በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል።

የነዋሪዎችን የልማት ጥያቄዎች የመለሱ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አዲሱ አስተዳደር አበክሮ መስራት እንዳለበትም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም