ቀጥታ፡

አቶ ኦርዲን በድሪ ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ

አዲስ አበባ  ፤ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ) ፦ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከመስከረም 21/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚሁ መሠረት፦ 

1ኛ ወይዘሮ ረምዚያ አብዱልወሃብ ቴክኒክና ሞያ ትምህርት እና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ

2ኛ ወይዘሮ ፈቲያ ሳኒ የሴቶችና ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ

3ኛ ወይዘሮ ፈሪሃ መሀመድ የሀረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምክትል ዲን

4ኛ አቶ ታመነ ፍቃድ የብቃት ማረጋገጫ ማዕከል ኃላፊ

5ኛ አቶ ረኢስ ዩሱፍ የሀረር ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ

6ኛ ኤልያስ ዩኒስ የሀረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ  ኃላፊ

7ኛ ዶ/ር አብዱልሀኪም ኢምራን ጀጎል ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ

8ኛ ወይዘሮ ሙና ኢስሀቅ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ባለስልጣን ኃላፊ

9ኛ አቶ ሰሚር አብዱላሂ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ

10ኛ አቶ አብዱልሀፊዝ አህመድ የሀረሪ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ኃላፊ

11ኛ አቶ ኤልያስ አብዱረህማን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ኃላፊ

12ኛ አቶ አብዱልሀኪም አብዱማሊክ የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ አደረጃጀት ጉዳይ አማካሪ

13ኛ አቶ ኃይለጊዮርጊስ መገርሣ የርዕሰ መስተዳድሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም