ቀጥታ፡

አቶ አደም ፋራህ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ) ፦ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ኢሬቻ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመከባበር፣ የዕርቅና የጠንካራ ማህበራዊ ትስስር እሴቶችን የሚያጎላ ታላቅ ባህላዊ መድረክ ነው።

በዓሉ ለሀገራችን ሰላም፣ ህብረብሔራዊ አንድነትና ብልጽግና የበለጠ እንድንተጋ ከፍተኛ መነቃቃትን የሚፈጥር እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።

#ትልቅ_ሀገር፣ #ትልቅ_ህዝብ፣#ታላቅ_ርዕይ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም