ቀጥታ፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የአስፈጻሚ አካላት ሹመት አጸደቀ

አርባምንጭ፤ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የአስፈጻሚ አካላት ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤውን በአርባ ምንጭ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ወቅትም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) አዲስ ለተመሰረተው የክልሉ ምክር ቤት ያቀረቧቸውን የአስፈጻሚ አካላት ሹመት ምክር ቤቱ ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ. ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) - የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

2ኛ. ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

3ኛ. አቶ ንጋቱ ዳንሳ - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

4ኛ. ካርታ ካስኬ (ዶ/ር) - የግብርና ቢሮ ኃላፊ

5ኛ. አቶ ዳዊት ደሳለኝ - ጤና ቢሮ ኃላፊ

6ኛ. ወ/ሮ ወይኒቱ መልኮ - የክልሉ ባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

7ኛ. መስፍን መንዛ (ዶ/ር) - የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

8ኛ. አቶ ሃይለማሪያም ተስፋዬ - የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ

9ኛ. አቶ ብርሃኑ ዘውዴ - የክልሉ ሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን ኃላፊ

10ኛ. አቶ ተፈሪ አባቴ - የክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

11ኛ. አቶ ታደለ ወልደሚካኤል - የክልሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

12ኛ. ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) - የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

13ኛ. አቶ መንግስቱ በየነ - ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ

14ኛ. አቶ ኤኬል ነትር - የክልሉ መስኖና ቆላማ ቢሮ ኃላፊ

15ኛ. ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ - ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

16ኛ. አቶ ሙሉቀን ታደሰ - የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ

17ኛ. ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ - የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

18ኛ. አቶ አቤነዘር ተረፈ - የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ

19ኛ. አቶ ተወልዴ ተስፋዬ - የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ

20ኛ. አልማዝ ባልታ (ዶ/ር) - የክልሉ ፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ

21ኛ. ሰለሞን ቡኬ (ዶ/ር) - የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ

22ኛ. አቶ ወንድማገኝ ደግፈ - የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመው ቃለ-መሐላ ፈፅመዋል።

በተጨማሪም አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ ቦጋለ ቦሼ (ዶ/ር) የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም አቶ ተስፋዬ ደፋሩ ደግሞ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም